Tuesday, December 17, 2013

የማይታይ ታይቶ

የማይታይ ታይቶ
ሰው ሁሉ ሲያደንቅሽ፣
ያልታየውን ቢያየው

እንዴት አይሞትልሽ።

በውጭው ውበት ላይ
ተደምሮ ውስጥሽ፣
በጣም ጎልቶ ታየ
ደመቀ ውበትሽ።

እድል ነው መታደል
አንቺ እድለኛ ነሽ፣
ሁለት ነገር ባንዴ
ፈጣሪ የቸረሽ።

ከነ ስራወችሽ
እንዲሁ እንዳለሽ፣
የሰማዩ አባት
ጠብቆ ያቆይሽ።

Wednesday, December 4, 2013

አማረኝ ! በተንጣለለ መሬት ላይ ነጭ ሽብሽብ አንሶላ አንጥፎ ከፍቅሬ ጋር መጋደም

አማረኝ !

በተንጣለለ መሬት ላይ ነጭ ሽብሽብ አንሶላ አንጥፎ ከፍቅሬ ጋር መጋደም -

በሀገራዊ ልብሶች ደምቄ ÷

በእጆቼ ወገብዋን እቅፍ አድርጌ በኮላ እንደተጣበቀ እንጨት 
ከውዴ ሰውነት ላይ ጥብቅ ብዬ

በአንድ እጄ ፊትዋን ማሻሸት አማረኝ


ስጎነትላት በነጠላዋ ጥለት ፊቶን ስትሸፍን እና ሀፍረቶን ስታሳየኝ ማየት አማረኝ


ተዝቆ ከማያልቀው ከዚህ ነጭ ሆኖ በተሸበሸበው ውብ ሜዳ ላይ ፍቅር ዘርቶ ፍቅር ማጨድ አማረኝ !!!

ከዚህ ሁሉ ሐተታ በኋላ ከአንዱ የአንሶላ እጥፋት ውስጥ የውድዬ ልብ መኖሩን ልብ አልኩኝ ::

ስዕሉ :- የሰዐሊ መዝገቡ ተሰማ ነው ::

ይህንን ያለችው  Rediet ነች !! ይህንን ስዕል አይቶ እንደስዋ አይነት ስሜት ያልተሰማው? መልካም ተፈጥሮ ስታይ ቦታው መሆንን የመሰለ ምኞት ግድ ይለናል!! ከዚህ ከቢጫ መጋረጃ ጀርባ ያለው ታሪክ እነኝህ ነጭ ለባሾች አይመስላችሁም ? ጥበብ አትንጠፍብህ !! አቦ እጆችህ ይባረኩ!! Mezgebu Tesema

እውነቴን ነው በፂ እኔም ከላይ ያልኩት ነገር አምሮኛል

 

//floating facebook like box
Don't Forget To Join Our Love Journey
Two Lovely years with Betselot and looking for 200 more years: love you
×

He is in Love!
//End of Facebook floating like box