Thursday, December 4, 2014

የናፈቅከኝ ለታ


የናፈቅከኝ ለታ This is for you Betsi .... this poem speaks my heart ... hope it will also speaks yours  

የናፈቅሽኝ ለታ ብለሽ አንብቢው thank you Mes Demoz


##### የናፈቅከኝ ለታ…#####
---------------------------------
የናፈቅከኝ ለታ…
ሳር ቅጠሉ ሁሉ አንተን ይመስለኛል
ከፊት ከኋላዬ ጎኔ የተቀመጥክ መስሎ ይሰማኛል።
የናፈቅከኝ ለታ…
የድምፅሕ ወለለት…
በእኩለ ሌሊት ገዝፎ ይሰማኛል፣
ባንቀላፋሁበት…
እንደ ዶሮ ጩኸት፣
እንደ ደብር ደውል፣
እንደ ወፍ ዝማሬ፣ ይቀሰቅሰኛል።
የናፈቅከኝ ለታ…
የሞቀው አልጋዬ…
እንደ ምድር ዋልታ
እንደሙት ሰውነት
እንደደጋን ቆፈን ይቀዘቅዘኛል፣
ለስላሳው አንሶላ
እንደ ደረቅ ቁርበት ይኮሰኩሰኛል።
የተመቸው ነገር ምቾት አይሰጠኝም፣
የጣፈጠው ምግብ
ጣዕሙ አይገባኝም።
( ውሃ እንኳ ያንቀኛል።)
አይገርምም?!
የናፈቅከኝ ለታ…
ጨዋታው ለዛ ቢስ
ሙዚቃው ሁካታ
ፀሐይዋ በረዶ
ቅዝቃዜው እቶን ሆኖ ይሰማኛል፣
ከተፈጥሮ አጋጭቶ
ከሰውኛ ህግጋት ገፍቶ ያስወጣኛል።
የናፈቅከኝ ለታ…
የጨረቃ ውበት አይስብ አይማርከኝ
የከዋክብት ብርሃን ከሉን አይገፍልኝ
ብቻ አንተን ብቻ አንተን አንተን እላለሁኝ።
ዳሩ ምን ዋጋ አለው…
ፀጉርህን ዳብሼ አቅፌ እንዳልስምህ
ድምፅህን እንዳልሰማ ናፍቄ እንዳላይህ
እልፍ ርቀኸኛል!
ህልም ሆነህብኛል!
ቢሆንም…
ወድሃለሁና ትናፍቀኛለህ
በሠዓት በደቂቃ ትዝ ትለኛለህ።
`ወድሃለሁና እናፍቅሃለሁ
ያውም ደስ እያለኝ፣
ተስፋ አለኝ ባንተ ደርሰህ እስክታክመኝ።
ደግሞ…እጠብቅሃለሁ!
ተከተይኝ በለኝ…
እስከዓለም ጥግጋት…
እስከዓለም ፍፃሜ…
ማቄን ጨርቄን ሣልል…እከተልሃለሁ!
ትናፍቀኛለህ…ውዴ…እወድሃለሁ!
* Mes Demoze
( ጥር 21 ቀን 2005 ዓ.ም)

Tuesday, March 18, 2014

አንደ'ዜ ተፃፊ

አንደ'ዜ ተፃፊ፥
ሺ ጊዜ ልቁጠርሽ፥
ሺ ጊዜ ልልቀምሽ፥
ሺ ጊዜ ልቅሰምሽ፤
እልፍ ጊዜ ላጥናሽ፣
እልፍ ጊዜ ግቢኝ፤
ታ'ምሮዬ ጓዳ፥ እልፍ ጊዜ ላግባሽ፤
እልፍ ጊዜ ላውጣሽ፤
ሺ ጊዜ ጠፍንጌ፥ እልፍ ጊዜ ልፍታሽ።
አንደ'ዜ ተሰፊ፥...
ሺ ጊዜ ልለካሽ፣
ሺ ጊዜ ላውልቅሽ፤
ሺ ጊዜ ልልበስሽ፣
እልፍ ልሙቅብሽ፣
እልፍ ልድመቅብሽ፣
ሺ ልሸልልብሽ፣
ሺ ልዘንጥብሽ፤
አንደ'ዜ ተሳዪ፥
ዘመን ዘላለሜን ካይንሽ ላፍጥብሽ፥
ካ'ይኔ ላይ ተተከይ፥
ከልቤ ተሰቀይ፥
ሺ ዓይን ይረፍብኝ
ሺ ዐይን ይረፍብሽ፤
እልፍ ይደመምብኝ፣
እልፍ ይደመምብሽ፤
የቀለም ቀንዴ ሆይ፥
ሺ ጊዜ ልጥቀስሽ፣
ሺ ጊዜ ልጥለቅሽ፤
እልፍ ላጊጥብሽ
እልፍ አውሬ ልውጋብሽ፤
የብሩሼ ጠጉር ስመላለስ ይለቅ፥
ያለፍሽበት ይርቀቅ፣
ያላየሽው ይድረቅ፥
መቃ ብሬ ይድመቅ፤
እልፍ አእላፍ ጊዜ፥ ባንቺ ልቀባባ፥
ቀለምሽ ተንጣፎ' ወደ ልቤ ይግባ፤
በነፋስ ተታለሽ፥ እንዲሁ ከምትደርቂ፣
አመድ ተደፍቶብሽ ላይኔ ከምትርቂ፥
ሸራው አእምሮዬ ይሰማመርብሽ፤
አቡጀዲው ቀልብሽ ይሸላለምልሽ፥
አንድ ጊዜ ማሪኝ፥ ሺ ጊዜ ልማርሽ።
/ዮሐንስ ሞላ/

Friday, January 31, 2014

እንደው ኑሮዬ ላይ ማቅራራት አምሮኝ ነበር …….. በፀፂየዬ የሚሰማኝን ነው የገጠመልኝ
  አሌክስ ደረሰልኝ

----|| ዘራፍ … ከበራፍ ! ||----------
------------------------------------(አሌክስ አብርሃም)

ትከሻሽ ለክንዴ ዙፋን
ጡቶችሽ ጠባቂ መላክ
ፀጉርሽ ጥቁር ፏፏቴ
ሳቅሽ ሃብል ላንገቴ
ፍቅርሽ የነብስ ድምቀቴ

አህዛብ ቁሞ ሲታዘብ
እቅፌ በትከሻሽ ሲያልፍ
ዘራፍ ! ፈሪ ባሉኝ ፊት
ዘራፍ ! በነብሴ በራፍ
ዘራፍ!!

ካለመኖርሽ በረሃ
ስትኖሪ መሬት ሰንጥቆ
የወጣ ቀዝቃዛ ውሃ
የነፍሰ ሃሴቴ ፍስሃ

መለየት ይሉት ጠላቴ
ላመታት ያፍገመገመኝ
መምጣትሽ እንደ ድንቅ ሃኪም
ከናፍቆት ደዌ ያከመኝ

ላመታት ያጎሳቆለኝ
ጨቋኙ ብቸኝነት ሲያልፍ
ዘራፍ በቃየው
ዘራፍ በደጃፍ !

እምቢ ለፍቅር
እንቢ ለመወድድ
ይሄን ጊዜ ነው
ጥላቻ እሚነድ
እምቢ !!!!!!

ጎረምሶቹ ቆንጆ እያቀፉ
በተራቆተ አይኔ ፊት ሲያልፉ
ልቤን በቅናት የሸነቆጠ
አቅፌሽ ቢያየኝ ተሸቆጠቆጠ
መከበሪያየ እንደዲሞፍተር
ደስታ መጣፊያ የነብሴ ደብተር
እቅፍ አርጌሽ ባደባባይ ሳልፍ
የፍቅር ልምጭ የመውደድ ጅራፍ
ከሰይጣን ጀርባ በጭካኔ ሲያርፍ
ዘራፍ
ዘራፍ
ዘራፍ በጓዳ ዘራፍ በደጃፍ !
የኔ ስንክሳር የመውደድ መጣፍ !
ዘራፍ !

ዲዳው መኝታ አፉ ሲፈታ
ቀጭ ግጥም ሲል የፍቅር ቃታ
ትራስ አንሶላው ሲተረማመስ
ምንጣፍ ብርድ ልብስ በጦር ሲታመስ
እንደደራሽ ወንዝ
ላብ በአንገት ዚጎርፍ
በትንፋሽ ዜማ ቅኔ ሲዘረፍ


በላብ ባህር ውስጥ መሻት ሲታመስ
መላ አካላችን እንደጣን ሲጨስ

አልጋ መደቡ ሲመስል አድዋ
ዋ……..እንደው …..ዘራፌዋ ….
እን……..ደው ዘራፌዋ !


!! thank you Alex Abreham

Wednesday, January 15, 2014

“የምትበላ ወፍ…”: ከምላሴ ጠጉር፤’ እሷን የመሰለ፤ መፈጠር አይችልም

“የምትበላ ወፍ…”

“ዉሰጅዉ ፍቅርሽን፤ እኔ አልፈልገዉም፣
ያንገላታል እንጂ፤ ሌላ ትርፍ የለዉም፣”

ይሉሻል በዘፈን፤ እነሱን አይደለሁ፤ ይህንን አልልም፣
ራሴን ነኝ እንጅ፣ አይን አይንሽን እያየሁ፤ አመታት የምቆም፣
ፀሎት ላምላክ ይዤ፤ ዘመናት የምፆም፣
የመ'ወ'ደድ አዚም፤ ስላለብሽ መስህብ፣
‘ያስተፈስ’ እያልኩኝ፤ ለሕይወቴ ቀለብ፣
ስምሽን 'ሰፍራለሁ፤ ጅብራዉን ሆኜ፤ ቆሜ ተገትሬ፤
ሲመሽም…፣ ሲነጋም…፤ አፍጥጬ…፣ አተኩሬ…፣

ፅጌ፣ ደመ ግቡ፤ መሆንሽን እያየሁ፣
ከኑሮዬ ይልቅ፤ አንቺን አጠናለሁ፣
እከርማለሁ እንጅ፤ ዉሰጅዉ አልልም፣
ቀዘባ፣ ከዘባ፤ ያልተሰራሽ ከደም፣
የዉበትም ቆሎ፤ በላይሽ የፈሰሰ፣
ስንቱ አንቺን ብሎ፤ ከስንቱ ደረሰ፣
ሸንቃጣ ዘበናይ፤ ግዳፍ የለሽ አጥንት፣
ባዘቶ ነስንሰሽ፤ ጉንጉን፣ የሰዉ እሸት፣
ሄድ መጣ ስትይ፤ ኪሊዮፓትራንም፤ ቅናት ሸንቁጧታል፣
ሞናሊዛም ቢሆን፤ የበለጣት ሲገኝ፤ በጣም ቆጭቷታል፣

ቢያምጡ፣ ቢወልዱ፤ እስከ ዘለ-አለም፣
‘ከምላሴ ጠጉር፤’ እንቺን የመሰለ፤ መፈጠር አይችልም፣
ቋጥኝ ድንጋይ ታርሶ፤ እህልም ቢበቅል፣
በማን መስፈርት፣ ዲካ፤ ዉበሽ ይለካል?
ቢያምጡ ቢወልዱ፤ እስከ ዝንተ-አለም፣
‘ከምላሴ ጠጉር፤’ እሷን የመሰለ፤ መፈጠር አይችልም።

በ ሱለይ አደም


 (በፀፂ ይህ ላንቺ ነው)

//floating facebook like box
Don't Forget To Join Our Love Journey
Two Lovely years with Betselot and looking for 200 more years: love you
×

He is in Love!
//End of Facebook floating like box