Wednesday, July 22, 2015

ጉድ! የሴት ልጅ ውበት! ቀሚስ የለበስሽ‘ለት!

( መላኩ_አላምረው )
…….
እየውልሽ ሔዋን ያንቺ ውበት ማለት
በቃ አንደኛ ነው! ቀሚስ የለበስሽ ‘ለት
* * * * * * *
እባክሽን ሔዋን ቀሚስሽን አክብሪው፣
ቀሚስ ስትለብሽ ነው እጅግ የምታምሪው፣
በቀሚስ ውስጥ ነው የምትፈቀሪው።
* * * * * * *
አመንዝራ ትውልድ ብልት መቁጠር
ሲያምረው፣
ሔዋን ያንችን ውበት ከቀሚስ አርቆ በሱሪ
ቀየረው፤
<<ጭራሽ 'ባለመረብ ታይት' ብሎ ሱሪ...
ተይ እንጅ ሔዋኔ... አንዳንዴማ እፈሪ !>>
* * * * * * *
ባንች ውስጥ ያለውን የእራሴን ገላ፣
የማንም ጉምዣታም በዓይኖቹ ሲበላ፤
በሄድሽበት ሁሉ ሲለክፍሽ ከሚውል፣
ምናለበት ገላሽ በቀሚስ ስር ቢውል?
* * * * * * *
አላወቅሽ እንዳይሆን....
ገላን በማጋለጥ በእይታ ያይደለ፣
ከልክፍት የራቀ ከመውደድ ከፍ ባለ፤
ኢትዮጵያዊ ሥሪት ይሄ ቀሚስ እኮ...
ወንድ ያንበረክክ ዘንድ በድንቅ ጥበብ
ማርኮ፣
ላንች የተሰጠ ለፍቅር ተባርኮ፤
የውበት ሰገነት የፍቅር ምሥጢር ነው፣
ቀሚስ የለበስሽ ለት ማያከብርሽ ማነው?
* * * * * * *
ሱስ ሆኖሽ ካልሆነ ያዳም ዘር ለከፋ፣
ምን ለብሰሽ ታውቂአለሽ - ከባለ መረቡ
ከ'ታይትሽ' የከፋ?
አንች እኮ ባንች ቤት፣
የተጋለጥሽ 'ለት...
የለከፋው ምሥጢር ውበቴ መስሎሻል...
በፍፁም አይደለም ማስተዋል ጎድሎሻል።
...>>>
አዳሜን በጉምዣት ልክፍት ያበደነው፣
ለዐውደ-ርእይ የዋለ ሐፍረተ-ሥጋሽ ነው።
(( እምብርትና ጡትሽ ተጋልጦ ከዋለ፣
ሌላ ያንች ሐፍረት ምን የቀረ አለ? ))
* * * * * * *
አትሰሚኝም እንጅ ብትሰሚኝማ፣
በልቤ ሚያነግሥሽ ልክ እንደኔ እማማ፤
ምሥጢረ ቁንጅና ጥበበ ሀበሻ፣
የሴትነት ድምቀት የወንድ ልብ ድል መንሻ፤
ይሄ ነው ያንች ልብስ ገመና ሸፋኙ፣
መራቆትን አይናፍቅ ይሄ ልብሽ ሞኙ።
ሚያምርብሽ ቀሚስ ነው ምን ነካሽ ወዳጄ፣
ይልቅ ለብሰሽና ብቅ በይ በደጄ።
* * * * * * *
ይኸው ልክ ነበርሁ…..
ይሄ ነው ውበትሽ ቀሚስ ያምርብሻል፣
ከበፊቱ ይልቅ ዛሬ ውብ ሆነሻል፤
አየሽኝልኝ አይደል ዓይኔ ሲንከራተት፣
ውብ ቀሚስ ብትለብሽ ውበትሽን ለማየት፤
አየሽኝልኝ አይደል ልቤ ሲደነግጥ፣
ቀሚስ ለሸፈነው ውበትሽ እጅ ሲሰጥ፤
* * * * * * *
ሔዋን ብሎ ክብር ቀሚስ ብሎ ውበት፣
ስትለብሽው አሳየኝ አሁን ነው ጉድ! ማለት፣
ከቀሚስ ጋር ሲሆን ጉድ! የሴት ልጅ ውበት።
* * * * * * *
//floating facebook like box
Don't Forget To Join Our Love Journey
Two Lovely years with Betselot and looking for 200 more years: love you
×

He is in Love!
//End of Facebook floating like box