ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር........
በፂ ምን ያህል እንደምወድሽ ደግሜ ደግሜ ነግሬሻለሁ…..
አንቺም እንደምትወጂኝ አውቃለሁ
አንቺን በማግኘቴ ደስታ በልቤ ውስጥ እንደ የማያቁዋርጥ
ጅረት እየፈሰሰ ነው
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር ... ፊቴ ፈገግ ይላል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር… አለም ለእኔ እየደነሰች
እንደሆነ ይሰማኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር … ብሩህ ተስፋ ይታየኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር…. ሳቅ ሳቅ ይለኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር …. እድለኝነት ይሰማኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር ….ፍቅር እንዲህ ነው ወይ
እንድል ያደርገኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር … ደስታ ይወረኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር … ተራርቆ መኖር ምን ያህል
ከባድ እንደሆነ ትዝ ይለኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር … ማፍቀር ምን ማለት እንደሆነ
ትዝ ይለኛል
ስንቺ ባሰብኩ ቁጥር … መፈቀር ምን ማለት እንደሆነ
ትዝ ይለኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር … ምንም ያልጎደለኝ እንደሆነ
ትዝ ይለኛል
ስላንቺ ባሰብኩ ቁጥር……….
በጣም እወድሻለሁ፣
በጣም አፈቅርሻለሁ
በጣም እደሰትችሻለሁ
Ti amo


